ንስር የማህበራዊ እድገትና የአካባቢ ጥበቃ የበጎ አድራጎት ማህበር (ንስር ሽልማት) በሀገሪቱ ህግ
መሰረት በድጋሚ በ2002ዓ.ም ተመዝግቦና ፍቃድ አግኝቶ የተቋቋመ ማህበር ሲሆን፤ ለትርፍ ያልተቋቋመ ህብረተሰብ አቀፍ ስራ የመስራትና
አእምሮ ግንባታን መሰረት ያደረገ ራዕይን የሰነቀ ነው፡፡
ለመቋቋም የማህበሩ መስራቾች በሀገራችን እየደበዘዘ የመጣውን የማድነቅና የማበረታት ባህል ዳግም እንዲያንሰራራ
መስራት እንዳለባቸው የወሰኑት፤ በሀገራችን በርካቶች እንኳን ለሀገራችን ለአህጉሪቱና ለዓለም የሚተርፍ በርካታ በጎ ስራዎችን ሰርተው
እያለ፤ በተቃራኒው የነበረንና ያጣንው “ጎሽ!” የማለት የማድነቅና የማበረታታት ባህላችን እየቀዘቀዘ በመምጣቱ ከማድነቅ ጀርባ ያለውን
ስኬት ትውልድ እንዳያጣጥመው ሳንካ መፈጠሩን በመገንዘብ ነው፡፡
“ማድነቅ በጎ ሰዎችን ብቻ አይደለም” የሚለው የማህበሩ ብሂል ከተፈጥሮ ጋር የተሳሰረ አካባቢን የማድነቅና
አካባቢን ከመጎዳት የመታደግ የአካባቢ ጥበቃ ስራም ሌላው ተግባሩ ነው፡፡ ሰው ከአካባቢው ጋር ተግባብቶና ተስማምቶ ሲኖር ዓለማችን
ሊኖራት የሚችለውን መልክ በመገመት የተለያዩ የሚመስሉ ነገር ግን የጋራ ጠባይ ላላቸው ዓላማዎች የተቋቋመም ማህበር ነው፡፡

No comments:
Post a Comment