Friday, February 27, 2015

ከ5ኛው የንስር ሽልማት ፕሮግራም ምን ይገኛል.....?

1.     ንስር ሽልማት ምንድን ነው?
ንስር ሽልማት በአካባቢ ጥበቃ፣ በቱሪዝም፣ በበጎ አድራጎትና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች አርያነት ያለው ስራ የሰሩ፣ ምግባራቸው ለብዙዎች የተቋምን ያክል ግንዛቤ ማስጨበጥ የሚችል፣ አንድ ሆነው ብዙዎች የማይሞክሩትን በመሞከር በመስራትና ሀገራቸውን በመጥቀም ድንቅ ተግባር ያከናወኑ ከሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ንስራዊ በሆነ ዓይን በመመልከት፣ አነጣጥሮ በማየት እውቅና የሚሰጥ የሀገር ልጅ የፈጠረው ቅን ልብ ነው፡፡
2.   የሽልማት ሥርዓቱ ገጽታ
ንስር ሽልማት የሚከናወነው በጎንደር ከተማ ሲሆን የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ እንደ ከዚህ ቀደሞች ሁሉ ሀገራዊ ይዘቶች ባሉት እሴቶች የታጀበ ነው፡፡ ዝግጅቱ ሶስት ዋና ዋና ምዕራፎች ሲኖረው፡-
1.      በዋንኛነት የሚከናወነው የሽልማት አሰጣጥ መርሐ ግብሩ ዋናውን ስፍራ ይይዛል
2.     ሌላው ተሸላሚው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ገጽ ለገጽ በመወያየት ልምዳቸውን የሚያጋሩበት ሲሆን
3.     ሶስተኛው ምእራፍ ከተሸላሚው ጋር በዘላቂነት ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ የተሸላሚውን ራእይ የሚያሰፉ የጋራ  ተግባራት  ላይ የሚደረገው ስምምነት ነው፡

    ከ5ኛው የንስር ሽልማት ፕሮግራም ምን ይገኛል.....

·         የ2007 ዓ.ም የንስር ሽልማት ስነ-ስርዕት በዶ/ር በርናርድ አንደርሰን (ሰው ማለት) ስም እንዲሆን በማድረግ ድንበር ተሻጋሪ ፍቅራቸውን እና ሙያዊ ውለታቸውን መዘከር ያስችላል
·         የሃገራችን በጎ አድራጊዎች እና ታሪክ ሰሪዎችን አመታዊ በሆነ መርሃ ግብር በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ሽልማታቸውን መውሰድ እንዲችሉ ይሆናል ይህም ይዚህችን የቀደመች ከተማ መልካም ገፅታ በስፋት ማስተዋወቅ ያስችላል
·         የ 2007 ዓ.ም የአካባቢ ጥበቃ ተሸላሚ ጋር የሶስት አመት የአምባሳደርነት ማዕረግ በመስጠት የጎንደር ከተማን ሳቢ ውብ እና አረንጓዴ ለማድረግ ያስችላል በዚህም የዳሽን ቢራ የአንበሳውን ድርሻ እንዲወጣ ያስችለዋል
·         ባልተለመደ ሁኔታ ተቋማዊ ስምምነቶች ይካሄዳሉ፡- በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ የስራ ውል ስምምነቶች በተሸላሚወች፤ በዳሽን ቢራ ፋብሪካ ፤ በአጋር ድርጅቶች እና በጎ/ከ/አስተዳደር መካከል ይደረጋል በዚህ አግባብ አንድም የባለራዕዩችን ራዕይ ማስፋት ሲያስችል (extending the visions of visionaries....) በሌላ መልኩ ደግሞ ከሽልማት በዘለለ ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ ተግባራትን ለመከወን ይቻላል
·         ንስር ሽልማት  መቀመጫውን ጎንደር ከተማ ያደረገ ቢሆንም ንስራዊ በሆነ ዓይን በሁሉም የሃገራችን ክፍሎች እየበረረ ሽልማት በመስጠት የሚያበረታታ እና ማህበረሰባዊ እድገት ላይ የሚያተኩር ፕሮጀክቶችን የሚከውን ግዙፍ ድርጅት
መፍጠር ያስችላል፡፡
·         እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት ከብዙ በጥቂቱ ናቸው...
Who is Next...?
 
1 comment:

  1. ጤና ይስጥልጥኝ፤ ሥርጉተ ሥላሴ እባላለሁ። የብዕር ስሜ ነው። በአማርኛውም በእግሊዘኛውም Seregute Selassie ብላችሁ ብትጎጉሉ ሁለመናዬን ታገኙታላችሁ። የ እንግሊዘኛው የ ዓለም አስፈሪነት እጅግ ስለሚከብደኝ ዓለም የፍቅርን ተፈጥሯዊ መርህ በትምህርት ቤት ደረጃ መስጠት አለበታ ብዬ ላውሬኢንስ የቃላት ፖስተር ክሊፕ የመሰራበት ነው። አማርኛው ደግሞ ሙግት ነው። aeger mnegede Kenebete ቀንበጥ አዲስ ብሎጌንም ብትጎበኙ ደስ ይለኛል። ሥርጉተ ሥላሴ የክርስትና ሥሜ ነው። በዓለማዊ ሥሜ ፈተና ሲበረክትብኝ ነው ሥርጉተ ሥላሴ የመረጥኩት። ዛሬ ስለ አንድ ባለድርብ ጭንቅላት ሰው ምርምር ሳደርግ ቁጭ ብዬ ነው ያደርኩት እና መንፈሴ ወስዶ ንስር ላይ አሳረፈኝ። ስለዚህም ንስር ተፈጥሮውን በጥልቀት ለማጥነት ዛሬን ለእሱ ማዋልን ፈቀድኩት። በዚህ ሂደት እናንተን ያገኘሁት። ስለምታደርጉት መልካም ነገር ሁሉ ላመሰግናችሁ አውዳለሁኝ። ቅዱስ ተግባር ነው። ኑሩልን። ንስርን መመረጣችሁ ብልህነታችሁን አሳይቶኛል። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ክብርም ኑሩላት።

    ReplyDelete