Friday, February 27, 2015

ከ5ኛው የንስር ሽልማት ፕሮግራም ምን ይገኛል.....?

1.     ንስር ሽልማት ምንድን ነው?
ንስር ሽልማት በአካባቢ ጥበቃ፣ በቱሪዝም፣ በበጎ አድራጎትና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች አርያነት ያለው ስራ የሰሩ፣ ምግባራቸው ለብዙዎች የተቋምን ያክል ግንዛቤ ማስጨበጥ የሚችል፣ አንድ ሆነው ብዙዎች የማይሞክሩትን በመሞከር በመስራትና ሀገራቸውን በመጥቀም ድንቅ ተግባር ያከናወኑ ከሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ንስራዊ በሆነ ዓይን በመመልከት፣ አነጣጥሮ በማየት እውቅና የሚሰጥ የሀገር ልጅ የፈጠረው ቅን ልብ ነው፡፡
2.   የሽልማት ሥርዓቱ ገጽታ
ንስር ሽልማት የሚከናወነው በጎንደር ከተማ ሲሆን የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ እንደ ከዚህ ቀደሞች ሁሉ ሀገራዊ ይዘቶች ባሉት እሴቶች የታጀበ ነው፡፡ ዝግጅቱ ሶስት ዋና ዋና ምዕራፎች ሲኖረው፡-
1.      በዋንኛነት የሚከናወነው የሽልማት አሰጣጥ መርሐ ግብሩ ዋናውን ስፍራ ይይዛል
2.     ሌላው ተሸላሚው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ገጽ ለገጽ በመወያየት ልምዳቸውን የሚያጋሩበት ሲሆን
3.     ሶስተኛው ምእራፍ ከተሸላሚው ጋር በዘላቂነት ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ የተሸላሚውን ራእይ የሚያሰፉ የጋራ  ተግባራት  ላይ የሚደረገው ስምምነት ነው፡

    ከ5ኛው የንስር ሽልማት ፕሮግራም ምን ይገኛል.....

·         የ2007 ዓ.ም የንስር ሽልማት ስነ-ስርዕት በዶ/ር በርናርድ አንደርሰን (ሰው ማለት) ስም እንዲሆን በማድረግ ድንበር ተሻጋሪ ፍቅራቸውን እና ሙያዊ ውለታቸውን መዘከር ያስችላል
·         የሃገራችን በጎ አድራጊዎች እና ታሪክ ሰሪዎችን አመታዊ በሆነ መርሃ ግብር በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ሽልማታቸውን መውሰድ እንዲችሉ ይሆናል ይህም ይዚህችን የቀደመች ከተማ መልካም ገፅታ በስፋት ማስተዋወቅ ያስችላል
·         የ 2007 ዓ.ም የአካባቢ ጥበቃ ተሸላሚ ጋር የሶስት አመት የአምባሳደርነት ማዕረግ በመስጠት የጎንደር ከተማን ሳቢ ውብ እና አረንጓዴ ለማድረግ ያስችላል በዚህም የዳሽን ቢራ የአንበሳውን ድርሻ እንዲወጣ ያስችለዋል
·         ባልተለመደ ሁኔታ ተቋማዊ ስምምነቶች ይካሄዳሉ፡- በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ የስራ ውል ስምምነቶች በተሸላሚወች፤ በዳሽን ቢራ ፋብሪካ ፤ በአጋር ድርጅቶች እና በጎ/ከ/አስተዳደር መካከል ይደረጋል በዚህ አግባብ አንድም የባለራዕዩችን ራዕይ ማስፋት ሲያስችል (extending the visions of visionaries....) በሌላ መልኩ ደግሞ ከሽልማት በዘለለ ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ ተግባራትን ለመከወን ይቻላል
·         ንስር ሽልማት  መቀመጫውን ጎንደር ከተማ ያደረገ ቢሆንም ንስራዊ በሆነ ዓይን በሁሉም የሃገራችን ክፍሎች እየበረረ ሽልማት በመስጠት የሚያበረታታ እና ማህበረሰባዊ እድገት ላይ የሚያተኩር ፕሮጀክቶችን የሚከውን ግዙፍ ድርጅት
መፍጠር ያስችላል፡፡
·         እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት ከብዙ በጥቂቱ ናቸው...
Who is Next...?
 
ንስር…!

ንስር የማህበራዊ እድገትና የአካባቢ ጥበቃ የበጎ አድራጎት ማህበር (ንስር ሽልማት) በሀገሪቱ ህግ መሰረት በድጋሚ በ2002ዓ.ም ተመዝግቦና ፍቃድ አግኝቶ የተቋቋመ ማህበር ሲሆን፤ ለትርፍ ያልተቋቋመ ህብረተሰብ አቀፍ ስራ የመስራትና አእምሮ ግንባታን መሰረት ያደረገ ራዕይን የሰነቀ ነው፡፡
ለመቋቋም የማህበሩ መስራቾች በሀገራችን እየደበዘዘ የመጣውን የማድነቅና የማበረታት ባህል ዳግም እንዲያንሰራራ መስራት እንዳለባቸው የወሰኑት፤ በሀገራችን በርካቶች እንኳን ለሀገራችን ለአህጉሪቱና ለዓለም የሚተርፍ በርካታ በጎ ስራዎችን ሰርተው እያለ፤ በተቃራኒው የነበረንና ያጣንው “ጎሽ!” የማለት የማድነቅና የማበረታታት ባህላችን እየቀዘቀዘ በመምጣቱ ከማድነቅ ጀርባ ያለውን ስኬት ትውልድ እንዳያጣጥመው ሳንካ መፈጠሩን በመገንዘብ ነው፡፡
“ማድነቅ በጎ ሰዎችን ብቻ አይደለም” የሚለው የማህበሩ ብሂል ከተፈጥሮ ጋር የተሳሰረ አካባቢን የማድነቅና አካባቢን ከመጎዳት የመታደግ የአካባቢ ጥበቃ ስራም ሌላው ተግባሩ ነው፡፡ ሰው ከአካባቢው ጋር ተግባብቶና ተስማምቶ ሲኖር ዓለማችን ሊኖራት የሚችለውን መልክ በመገመት የተለያዩ የሚመስሉ ነገር ግን የጋራ ጠባይ ላላቸው ዓላማዎች የተቋቋመም ማህበር ነው፡፡